በኢትዮጵያ ወታደራዊ አካዳሚው የ70ኛ ጊዜ ተወዳዳሪ እጩ መኮንኖች አመታዊ የስፖርት ፌስቲቫል ተጀመረ፡፡

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

ህዳር 2 ቀን 2015 ዓ.ም

በኢትዮጵያ ወታደራዊ አካዳሚው የ70ኛ ጊዜ ተወዳዳሪ እጩ መኮንኖች አመታዊ የስፖርት ፌስቲቫል ተጀመረ፡፡

ዕጩ መኮንኖቹ ከትምህርታቸው ጎን ለጎን የሚሰጠውን የተጓዳኝ ስርዓተ ትምህርት መሰረት በማድረግ የተጀመረው የስፖርት ፌስቲቫል የተለያዩ አይነት ውድድሮችን የያዘ ሲሆን በእግር ኳስ፣ በገመድ ጉተታ፣ በካርታ ንባብ፣ በ3 ኪ.ሜ ሩጫ፣ በተኩስና በመሳሰሉት የውድድር አይነቶች ይከናወናል፡፡

በመክፈቻ ስነስርአቱ ላይ በመገኘት ንግግር ያደረጉትና ውድድሩን በይፋ ያስጀመሩት የኢትዮጵያ ወታደራዊ አካዳሚ አዛዥ ብ/ጄ ጌታቸው አሊ ስፖርት የሰልጣኝ ዕጩ መኮነኑን ስነ ልቦና ከፍ በማድረግ፣ እርስ በእርስ በማቀራረብ፣ ጠንካራ ዝምድና እና አንድነት በሰልጣኞች መካከል ለመፍጠር ያስችላል ብለዋል፡፡

አካዳሚው ዕጩ መኮነን ሰልጣኞችን ከማስተማር ጎን ለጎን እንደ መደበኛ ስራ ከሚያከናውናቸው አበይት ተግባራት ውስጥ አንዱና ዋንኛው ስፖርት መሆኑንም ብ/ጄ ጌታቸዉ ተናግረዋል፡፡