ስፖርት ለሰላምና ለአንድነት" በሚል መሪ ቃል በዋግኽምራ ብሔረሰብ ዞን በተደረገው የስፖርት ውድድር በዕዙ ቡድን አሸናፊነት ተጠናቀቀ።

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

ነሐሴ 12 ቀን 2014 ዓ.ም

"ስፖርት ለሰላምና ለአንድነት" በሚል መሪ ቃል በዋግኽምራ ብሔረሰብ ዞን በተደረገው የስፖርት ውድድር በዕዙ ቡድን አሸናፊነት ተጠናቀቀ።

በዋግኽምራ ቤሄረሰብ አስተዳደር የመንግስት መስርያ ቤቶች እና በፀጥታ አካላት የተደረገው ውድድር ሰራዊቱን እና ማህበረሰቡን ያቀራረበ፣ የእርስ በርስ ግንኙነትን ያጠናከረ እና ጠላትን በጋራ እንድንመክት ያስተሳሰረን ነው ሲሉ የዞኑ ወጣቶችና ስፖርት ኃላፊ አቶ መኮንን ዘገዬ ገልፀዋል።

የዕዙ ስነ ልቦና ግንባታ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ተወካይ ሌ/ኮ ለችሳ መገርሳ በበኩላችው ሰራዊቱ ከግዳጁ ጎን ለጎን ከማህበረሰቡ ጋር የሚያደርገው ስፖርታዊ ውድድር አንድነታችንን ያሳዬ ነው። ወታደርና ስፖርት የማይለያዩ ፤ ስፖርት የዕለት ከዕለት ስራችን በመሆኑም በተደረገው ውድድር ዕዛችን የዋንጫ ባለቤት መሆን ችሏል ብለዋል።

መቶ አለቃ አንበሴ ድርቢሳ በበኩላቸው ዞኑ ለውድድር ካዘጋጃቸው 3 ዋንጫዎች ሁለቱን ዋንጫዎች በመረብ ኳስ እና በእግር ኳስ በማሸነፍ ወስዷል። በዚህም በጣም ደስተኞች ነን ሲል ተናግሯል።

ልመንህ ሻውል

ፎቶግራፍ ዳንኤል ጌቱ

ተጨማሪ መረጃዎች ከታች ያሉትን ሊንኮች ይጠቀሙ።