መርሆዎች
የመከላከያ ሰራዊት ህገ-መንግስታዊ መርሆዎች
የመከላከያ ሰራዊት ህገ-መንግስታዊ መርሆዎች
- የሀገሪቱ የመከላከያ ሠራዊት የብሔሮች፣ የብሔረሰቦች እና የሕዝቦችን ሚዛናዊ ተዋጽኦ ያካተተ ይሆናል፡፡
- የመከላከያ ሚኒስትር ሆኖ የሚሾመው ሲቪል ይሆናል፡፡
- የመከላከያ ሠራዊት የሀገሪቱን ሉዓላዊነት ከመጠበቅ በተጨማሪ በሕገ-መንግስቱ መሰረት በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የሚሰጡትን ተግባሮች ያከናውናል፡፡
- የመከላከያ ሠራዊቱ በማናቸውም ጊዜ ለሕገ-መንግስቱ ተገዢ ይሆናል፡፡
- የመከላከያ ሠራዊቱ ተግባሩን ከፖለቲካ ድርጅቶች ወገናዊነት ነጻ በሆነ አኳኋን ያከናውናል፡፡