የኢፌዴሪ መከላከያ ራዕይ

የኢፌዴሪ መከላከያ ራዕይ

ለህገ-መንግስቱና ለህገ-መንግስታዊ ሥርዓቱ ፍፁም ታማኝ የሆነ፤ የሀገራችን ህዝቦች ተምሣሌነት የህዝብ አመኔታንና ፍቅርን የተጐናፀፈ፤ የዕውቀት መፍለቂያ፤ ጦርነትን ማስቀረት የሚችል፤ ካጋጠመም አስተማማኝ የማሸነፍ ብቃት ያለው፤ በአህጉራዊና በዓለም አቀፋዊ ግዳጅ ግንባር ቀደም ሚና የሚጫወት ዘመናዊ የመከላከያ ኃይል ተገንብቶ ማየት፣

 

የመከላከያ ሰራዊት ተልዕኮዎች

1. ሀገሪቱን እና ሕገ-መንግስታዊ ሥርዓቱን ከውጭ ወራሪ ኃይሎች፣ ሽብርተኞች እና ከውስጥ ፀረ-ሰላም ኃይሎች በአስተማማኝ ሁኔታ በመከላከል የሀገሪቱ ሰላም እንዲጠበቅና የፈጣን ልማትና የዲሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ እንቅስቃሴ ያለ እንቅፋት እንዲቀጥል ማድረግ ፤

2. አግባብነት ያላቸው የክልል መስተዳድር የደህንነትና የፀጥታ መዋቅሮችን የደህንነትና የፀጥታ ማስከበር አቅማቸውን መገንባትና ከእነርሱ ጋር ተቀናጅቶ መስራት ፤

3. የሀገሪቱን ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች የሕዝብና የመንግስት የልማት ተቋማትንና አውታሮችን ከማንኛውም ሰው ሰራሽና ተፈጥሮአዊ አደጋዎች መከላከል እና ማዳን ፤

4.ሀገራዊ ደህንነትን ማረጋገጥና በከባቢያዊ ፣ አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ የሰላም ማስከበር ተልዕኮዎች ላይ በብቃት መሳተፍ ፡፡

 

የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ቁልፍ እሴቶች

            1. ከራስ በፊት ለሕዝብና ለሀገር ጥቅም ፤

2. ምንጊዜም የተሟላ ስብዕና ፤

              3. ያልተሸራረፈ ዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብ ፤

                          4. በማንኛውም ግዳጅ ወይም ተግባር የላቀ ውጤት ፡፡