Asset Publisher

null በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአብዬ ጊዜያዊ ሰላም አስከባሪ ሀይል ኢንስፔክሽን ምክትል ሀላፊ በሚስተር ዲሚትሪ ሶቦልቨስኪ የተመራው ልዑካን ቡደን በ9ነኛ ዙር ቀላል መሀንዲስ ሻምበል የመጀመሪያ ዙር ኢንስፔክሽን አካሄደ ።

ልኡካን ቡድኑ የሻምበሉን ተተኳሽ ትጥቆች ጨምሮ ፣ ተሽከርካሪዎችን ፣ የመንገድና የቤት መቀየሻ የምህንድስና መሳሪያዎችን ፣ የዉሀ መሳቢያ ፓምፖችን ፣ የአፈር መመርመሪያ ላቦራቶሪ ክፍል ፣ የውሀ ማጣሪያ ማሽነሪዎችን ፣ የማሽነሪ ግምጃ ቤቶችን የሰራዊቱን መመገቢያ አዳራሽ እና ሌሎችን የሻምበሉን ክፍሎች በመዘዋወር ፍተሻ አካሂዷል።
ሻምበሉ በተሟላ ወታደራዊ ቁመና ላይ እንደሚገኝ ማረጋገጣቸውን የተናገሩት ሚስተር ዲሜትሪ ፣ በተለይም ዋነኛ መገልገያ ንብረቶች መቶ ፐርሰንት ዝግጁ መሆናቸውን ነው የገለፁት።
የሻምበል አዛዡ ሻለቃ ተመስገን ጌታቸው በበኩላቸው ፣ በመንግስታቱ ድርጅት የተሰጠንን ተልዕኮ ለመፈፀም እና ሀገራችን ከዘርፉ የምታገኘውን ጥቅም ለማስጠበቅ ከሀይል ውጭ የነበሩ ተሽከርካሪዎችን ጭምር በመጠገን ከፍተኛ ዝግጅት አድርገናል ነው ያሉት።
በላቸው ክንዴ
ፎቶግራፍ ማሩ ግርማይ