ጥቂቶቹ "በሚል ርዕስ በአቶ አለማየሁ ማሞ የተዘጋጀው መፅሃፍ በሀገር ፍቅር ቲያትር ቤት ተመረቀ።

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

ህዳር 3 ቀን 2015 ዓ.ም

ጥቂቶቹ "በሚል ርዕስ በአቶ አለማየሁ ማሞ የተዘጋጀው መፅሃፍ በሀገር ፍቅር ቲያትር ቤት ተመረቀ።

በምረቃ ፕሮግራሙ የተገኙት የቀድሞው የኢትዮጵያ ባህር ሃይል አንድነት ማህበር ተወካይ ካፕቴን መዝገበ ወርቄ "ጥቂቶቹ "በሚል ርዕስ የተዘጋጀው መፅሃፍ የኢትዮጵያን ባህር ሃይል አባላት አስደናቂ ግለ ታሪኮች የህይወት ውጣ ውረዶችን እና ጀግንነትን የሚገልፅ ነው።

መፅሃፉ ስለ ኢትዮጵያ ባህር ሃይል አመሰራረት ታሪክ እንዲሁም ኢትዮጵያ ባህር ሃይል አልባ እስከሆነችበት 1991 እ.ኤ.አ ስለነበረው ሁለገብ ተሳትፎም በርካታ ቁም ነገሮችን እንዲሁም ኩነቶች ሰንዶ የያዘ ነው። ይህ መፅሀፍ ለተተኪው ትውልድ አስተማሪ እና ለምርምር መነሻ ይሆናል ።ስለዚህ ደራሲው ይህን ታላቅ ስራ ማበርከቱ ሊመሰገን ይገባል ሲሉ ካፒቴን መዝገበ ወርቄ ተናግረዋል ።

የኢትዮጵያ ባህር ሃይል ምክትል አዛዥ ለሎጀስቲክስ ኮሞደር ዋለፃ ዋቻ በበኩላቸው ባህር ሀይል እንደ አንድ የመከላከያ ሃይል ሆኖ እንዲደራጅ በየደረጃው የሚገኝ አመራርና አባላት የማሟላት ስራ ባለፈው አራት አመታት መከናወኑን ገልፀው እስከ አሁን ለተመዘገቡት ስኬቶች የቀደሞ ባህር ሃይል አባላት ድጋፍ የታከለበት በመሆኑ ምስጋናዬ ከፍ ያለ ነው ሲሉ ምስጋናቸውን በባህር ሃይል ስም አቅርበዋል።

ከመፃፉ ሽያጭ የሚገኘው ገንዘብ የቀድሞ የኢትዮጽያ ባህር ሃይል አባለት ለነበሩ እና በችግር ላይ ለሚገኙ ድጋፍ እንዲሆን መወሰኑን የመፅሃፉ ደራሲ አቶ አለማየሁ ማሞ ተናግረዋል ።

ማሙሸት አድነው

ፎቶግራፍ ማሙሸት አድነው