የኢፌዴሪ የመከላከያ ሰራዊት ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ የቻይና የመከላከያ ሰራዊት የተመሰረተበትን 95ኛ አመት ክብረ በዓል በማስመልከት የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት አስተላለፉ፡፡

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]
ሐምሌ 27 ቀን 2014 ዓ.ም
የኢፌዴሪ የመከላከያ ሰራዊት ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ የቻይና የመከላከያ ሰራዊት የተመሰረተበትን 95ኛ አመት ክብረ በዓል በማስመልከት የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት አስተላለፉ፡፡
ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ፣ ባስተላለፉት መልዕክት የቻይና የመከላከያ ሰራዊት የሀገሩን ሉአላዊነት፣ ፀጥታና ጥቅም ከማስከበር አልፎ ለአለማችን ሰላምና መረጋጋት እያደረገ ላለው በጎ ሚና ያላቸውን አድናቆት ገልፀዋል፡፡
ቻይናና ኢትዮጵያ ለረጅም ዘመናት የዘለቀ ታሪካዊ ወዳጅነት እንዳላቸው ያወሱት ጠቅላይ ኢታማዦር ሹሙ ፤ በጋራ ተጠቃሚነት ላይ በመመስረት በሀገራቱ መካከል ያለው ግንኙነት በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚ፣ በባህል፣ በትምህርት እና በጤና መስኮች ከፍተኛ ዕድገት እያሳየ መምጣቱን ገልፀዋል፡፡
ሁለቱ ወዳጅ ሀገራት በወታደራዊ ዲፕሎማሲና ትብብር ላይ ከፍተኛ ዕድገት ላይ እንደደረሱ የገለፁት ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ ያላቸውን ትብብር ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ እየተሰራም እንደሚገኝ አረጋግጠዋል፡፡
ብዙአየሁ ተሾመ
ፎቶግራፍ በሀይሉ ስለሺ