የመከላከያ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር አብርሃም በላይ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት፦ ይህ ዓመት፥ የህዳሴ ግድብ ፕሮጀክታችን፣ በብዙ መለኪያዎች አጥጋቢ እመርታዎችን ያስገኘንበትና ወደ ወሳኝ የማገባደጃ ምእራፍ የሚያደርሱንን ስራዎች ያጠናቀቅንበት ዓመት ነበር ማለት እንችላለን::

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]
ነሐሴ 6 ቀን 2014 ዓ.ም
የመከላከያ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር አብርሃም በላይ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት፦
ይህ ዓመት፥ የህዳሴ ግድብ ፕሮጀክታችን፣ በብዙ መለኪያዎች አጥጋቢ እመርታዎችን ያስገኘንበትና ወደ ወሳኝ የማገባደጃ ምእራፍ የሚያደርሱንን ስራዎች ያጠናቀቅንበት ዓመት ነበር ማለት እንችላለን::
ይኸውም ከፕሮጀክቱ ለማግኘት ያቀድነውን ኃይል በማመንጨት፤ የህዳሴን ፍሬ ማየትና ማጣጣም የጀመርንበት፣ የግድቡ መካከለኛው ክፍል 600 ሜ ፣ እንዲሁም ግራና ቀኝ ያለውን ክፍልም 611 ሜ ከባህር ወለል ከፍታ በላይ በመድረስ፣ ሁለት የቅድመ ኃይል ማመንጫ ጀነሬተሮች ኃይል እንዲያመነጩ ማድረግ የቻልንበትና 22 ቢ.ሜ.ኪ ውሀ የያዝንበት የድል ዓመት መሆኑን ስናበስር፥ ለዚህ ፕሮጀክት መሳካት ሁለንተናቸውን ለሰጡ፣ ለኢትዮጵያ ህዝብ እና መንግስት ሌላ የከፍታ እርከን ሆኖ በታሪክ ተመዝግቧል::
ይህንን ውጤት የተገኘው፣
የግድቡ ግንባታ ስራ እዚህ እንዳይደርስ የውጭ ጠላቶችና የውስጥ ተላላኪ ባንዳዎች ተቀናጅተው ከፍተኛ መዋለ-ነዋይ በማፍሰስ አመቱን ሙሉ ያለ እረፍት፣ በሁሉም አይነት መንገድ መሰናክሎችን ደርድረው እንዲስተጓጎል በተንቀሳቀሱበት ዓመት ነው። ሆኖም ፈተናዎቹን በፅናት አልፈን ወሳኝ ስራዎችን ሰርተን ለከፍተኛ ውጤት ደርሰናል። በዚሁም ለጠላቶቻችን እንደማንበገር በቂ መልእክት፤ ለህዝባችን ደግሞ የፅናት ውጤት ማሳያ ነው።
ይህ የላቀ ውጤት እንዲገኝ፥ ሁሉም የፀጥታ አካላት፣ በተለይ ደግሞ ጀግናው የሀገር መከላከያ ሰራዊታችን ለግድቡ የሚያስፈልግ የግንባታ ግብአት አቅርቦት ለአፍታም ሳይስተጓጎል እንዲቀርብ፣ ከስሚንቶ ፋብሪካ እስከ ግድቡ ድረስ ያለውን የተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ ከፀረ ልማትና ፀረ ሰላም ሀይሎች በመጠበቅ፣ በመቶ ኪሎ-ሜትሮችን በእግር እያጀበና መንገድ እያፀዳ መስዋእትነትም ጭምር እየከፈለ፣ የተበላሹ መንገዶችን በራሱ እየጠገነ፣ የግብአት አቅርቦት እንቅስቃሴው በበጋም በክረምትም ሳይቆራረጥ ስራው እንዲሰራ በማድረጉ ነው::
በተጨማሪም፣ ፕሮጀክቱ መንግስት ያስቀመጠውን እጅግ በጣም የተለጠጠ አመታዊ እቅድ እንዲሳካ ጥብቅ አመራር በመስጠት ክትትልና ድጋፍ ላደረጉ የመንግስት ሀላፊዎች ፣ የቦርድ አመራር አባላት ፣ የመብራት ኃይል አመራርና ሰራተኞች ፣ በፕሮጀክቱ የሚሰሩ ኮንትራክተሮችና ሁሉም ሰራተኞች ያለ እረፍት ሌት-ተቀን በመስራታቸው እና ተገቢ አመራር በመስጠታቸው የተገኘ ውጤት ነውና እናመሰግናቸዋለን::
እንዲሁም የደርባ ስሚንቶ ፋብሪካ አመራርና ሰራተኞች፣ በግብአት አቅርቦት ሂደት የተሳተፋቹ የመንግስትና የግል ትራንስፓርተሮች የግብአት አቅርቦቱ በሚፈለገው ደረጃ እንዲሟላ ልዩ ትኩረትና አመራር በመስጠታቹ የተገኘ ውጤት ነውና እናመሰግናለን ::
ቀጣይ ቀሪ ዓመታትም ቢሆን፣ የሚቀመጡትን አመታዊ ግቦች በማሳካት ብሎም ፕሮጀክቱ ሙሉ በሙሉ ማጠናቀቅ የሚቻለው የናንተ ድጋፍና ትብብር ሲታከልበት በመሆኑ፣ በተገኘው ውጤት ሳንዘናጋ ፕሮጀክቱ እስኪጠናቀቅ ድረስ አብረን እንድንጓዝ ጥሪዬን አአቀርባለ::