"ኢትዮጵያ ለዓለምና ለቀጠናው ሰላምና መረጋጋት የምታደርገውን ጥረት አጠናክራ ትቀጥላለች፡፡" የኢፌዴሪ የመከላከያ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር አብርሀም በላይ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]
ሐምሌ 27 ቀን 2014 ዓ.ም
"ኢትዮጵያ ለዓለምና ለቀጠናው ሰላምና መረጋጋት የምታደርገውን ጥረት አጠናክራ ትቀጥላለች፡፡" የኢፌዴሪ የመከላከያ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር አብርሀም በላይ
በቻይና አዘጋጅነት በተካሄደው የቻይና-አፍሪካ የሚኒስትሮች የሰላምና የፀጥታ ፎረም ላይ በመሳተፍ መልዕክታቸውን ያስተላለፉት የኢፌዴሪ የመከላከያ ሚኒስቴር ሚንስትር ዶ/ር አብርሀም በላይ ወቅቱ በአለማችን ሆነ በአካባቢያችን የሚታዩ የፀጥታ ችግሮችን ለመቅረፍ ከሰላም ሀይሎች ጋር በትብብር መስራት የሚያስፈልግበት ጊዜ ነው ብለዋል፡፡
የቀደምት ስልጣኔ ባለቤት የሆነችው ሀገራችን ኢትዮጵያም በፓን-አፍሪካን መንፈስ አፍሪካዊ ችግሮችን በአፍሪካውያን ለመፍታት እንዲቻል በፅናት እየሰራች መሆኗን ገልፀው የቻይና ሪፐብሊክ መንግስትም አካታችና ሚዛናዊ አካሄድን በመከተል ለአለም ሰላምና መረጋጋት እያደረገ ላለው ሚና ያላቸውን ክብርና አድናቆት ገልፀዋል፡፡
“የጋራ ደህንነትን ለማረጋገጥ አብሮነትና ቅንጅትን ማጠናከር ይገባል::” በሚል መርህ በተካሄደው ሁለተኛው የቻይና-አፍሪካ የሚኒስትሮች የሰላምና የፀጥታ ፎረም ከሀምሳ በላይ ሚኒስትሮችና የአፍሪካ ህብረት ተወካዮች ተሳትፈዋል፡፡
ብዙአየሁ ተሾመ
ፎቶግራፍ ተሰማ ኡርጌሳ