መከላከያ በ18ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ሀገራቸውን በዓለም መድረክ ከፍ አድርገው ላስጠሩ አትሌቶች አቀባበል አደረገ።

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]
ሐምሌ 21 ቀን 2014 ዓ.ም
መከላከያ በ18ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ሀገራቸውን በዓለም መድረክ ከፍ አድርገው ላስጠሩ አትሌቶች አቀባበል አደረገ።
አትሌቶቹ ፈተናዎችን ተቋቁመውና ጠንክረው ሰርተው ላስመዘገቡት ድል የሀገር መከላከያ ሚኒስቴር ከፍተኛ ምስጋና አቅርቦላቸዋል።
በአቀባበል ስነ ሥርዓቱ ላይ የመከላከያ ሚኒስትር ዶ/ር አብርሃም በላይን ጨምሮ ም/ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጀኔራል አበባው ታደሰ፣ ጀኔራል መኮንኖች እና ተጋባዥ እንግዶች የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
እንደ ሀገር በተገኘው ድል ላይ የመከላከያ አትሌቶች የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዳበረከቱም ተገልጿል።
አትሌቶች ከምንም በላይ ሀገርን በማስቀደም ከፍተኛ ተጋድሎ ማድረጋቸውን የገለፁት የመከላከያ ሚኒስትር ዶ/ር አብርሃም በላይ ፈተናዎችን ተቋቁመው በመሥራታቸው ከፍተኛ ውጤት ማስመዝገባቸውን ተናግረዋል።
በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች በአንድነት በመሰለፍ ያሳዩት ብቃት የሚደነቅና የሚመሰገን እንደሆነም ሚንስትሩ ዶ/ር አብርሃም በላይ ገልፀዋል።
አስተያየታቸውን የሰጡት የመከላከያ ሠራዊት አባላትም አትሌቶቻችን ያስመዘገቡት ድል ሀገርን ያኮራና አንድነትን ይበልጥ ያጠናከረ ነው ብለዋል።
ለ18ኛ ጊዜ በአሜሪካ ኦሪገን በተካሄደው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ 4 ወርቅ፣ 4 ብር፣ 2 ነሐስ የተገኘ ሲሆነ ከዚህ ውስጥ የመቻል አትሌቲክስ ቡድን በሴቶች 3000 ሜ መሰናክል መሰረታዊ ወታደር ወርቅውሀ ጌታቸው የብር ሜዳል፤ በ5000 ሜ ሃምሳ አለቃ ዳዊት ስዩም የነሐስ ሜዳሊያ ማግኘታቸው ይታወቃል።
ውብሸት አንበሴ