ሙዚቃና ቴአትር ቡድኑ ሠራዊታችን ግዳጁን በብቃት እንዲፈፅም የራሱን ሚና ተወጥቷል። የምስራቅ ዕዝ ሙዚቃና ቴአትር ቡድን ኃላፊ ሌ/ኮ ጋሻው ንጉሴ - Ministry of Defense
ሙዚቃና ቴአትር ቡድኑ ሠራዊታችን ግዳጁን በብቃት እንዲፈፅም የራሱን ሚና ተወጥቷል። የምስራቅ ዕዝ ሙዚቃና ቴአትር ቡድን ኃላፊ ሌ/ኮ ጋሻው ንጉሴ
ግንቦት 16 ቀን 2014 ዓ.ም
ሙዚቃና ቴአትር ቡድኑ ሠራዊታችን ግዳጁን በብቃት እንዲፈፅም የራሱን ሚና ተወጥቷል። የምስራቅ ዕዝ ሙዚቃና ቴአትር ቡድን ኃላፊ ሌ/ኮ ጋሻው ንጉሴ
ሠራዊቱ የሚሰጠውን ተልዕኮ በሚገባ እንዲፈፅም ሙዚቃና ቴአትር ቡድኑ በግዳጅ ቀጠና ተንቀሳቅሶ የማነሳሳትና የግንባታ ስራዎችን አከናውኗል።
የምስራቅ ዕዝ ሙዚቃና ቴአትር ቡድን ኃላፊ ሌ/ኮ ጋሻው ንጉሴ እንደተናገሩት ኪነት ቡድኑ ከጊዜ ወደ ጊዜ እራሱን በማብቃትና በማሻሻል ሠራዊቱ በሚገኝባቸው ግንባሮች ድረስ በመንቀሳቀስ የተጣለበትን ሃገር የማስከበር ተልዕኮውን ደስተኛ ሆኖ እንዲፈፅም ለማስቻል ሞራልና ስነ- ልቦናውን ከፍ የማድረግ ስራዎች መከናዎናቸውን ገልፀዋል።
ሙዚቃና ቴአትር ቡድኑ ባቀረበው የሙዚቃ መድረክ ሠራዊቱ ደስተኛ መሆኑንና ቀጣይ ለሚሰጠው ግዳጅ ትልቅ የሞራል ስንቅ እንደገነባ በመድረኩ ተገልጿል።
ሃሰን ጀማል
ፎቶግራፍ ይቅርታ ብዙአየሁ