በጋዜጠኛና ገጣሚ ሻለቃ ፈይሳ ናኔቻ ተፅፎ ለምረቃ የበቃው የግጥም መድብል በ183 ገፆች የተዘጋጀ ሲሆን የተለያዩ ወታደራዊና ማህበራዊ ጉዳዮችን የሚዳስስ ነው።

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

ሰኔ 25 ቀን 2014 ዓ.ም

"ብዕር ከጠብ-መንጃ" የተሰኘ የግጥም መድብል ተመረቀ።

በጋዜጠኛና ገጣሚ ሻለቃ ፈይሳ ናኔቻ ተፅፎ ለምረቃ የበቃው የግጥም መድብል በ183 ገፆች የተዘጋጀ ሲሆን የተለያዩ ወታደራዊና ማህበራዊ ጉዳዮችን የሚዳስስ ነው።

ጋዜጠኛና ገጣሚ ሻለቃ ፈይሳ ናኔቻ በመከላከያ ሰራዊቱ ውስጥ በሚፅፋቸው የተለያዩ አጫጭር መጣጥፎችና ግጥሞች ተወዳጅ የሆነ ጋዜጠኛና ገጣሚ ነው።

በዕለቱ በሀገራችን ታዋቂ ሰዎች ከመፅሐፉ የተመረጡ ግጥሞችን ለንባብ ያበቁ ሲሆን የመከላከያ የሙዚቃ ኦርኬስትራ ባንድ የተለያዩ ጥዑመ ዜማዎች በማቅረብ ለምረቃ ስነ-ስርአቱ ድምቀት ሰጥቶታል።

በዝግጅቱ ላይ የመከላከያ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክትሬት ዳይሬክተር ኮ/ል ጌትነት አዳነን ጨምሮ ከፍተኛ የሰራዊቱ አመራሮች፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችና የገጣሚው አድናቂዎች ተገኝተዋል።

ብዙአየሁ ተሾመ

ፎቶግራፍ ተሰማ ኡርጌሳ