ኢትዮጵያ በአለም አቀፍ የሰላም ማስከበር ተሳትፎ ያላትን የላቀ አስተዋፅኦ ሌሎች ሀገራት ሊቀስሙት እንደሚገባም ተገለፀ፡፡

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

ህዳር 15 ቀን 2015 ዓ.ም

ኢትዮጵያ በአለም አቀፍ የሰላም ማስከበር ተሳትፎ ያላትን የላቀ አስተዋፅኦ ሌሎች ሀገራት ሊቀስሙት እንደሚገባም ተገለፀ፡፡

የጃፓን አለም አቀፍ የሰላም ትብብር ሴክሬታሪያት ዳይሬክተር ጄኔራል ሚስተር ካኖ ታኬሮ የተመራ ልኡክ ቡድን በመከላከያ ሰላም ማስከበር ማዕከል አለም አቀፍ ሰላም ማስከበር ማሰልጠኛ ተቋምን ጎበኝቷል፡፡

የመከላከያ ሰላም ማስከበር ማእከል አዛዥ ሜጄር ጄኔራል አዳምነህ መንግስቴ የኢትዮጵያና የጃፓን ወዳጅነት ረጅም እድሜ ያስቆጠረ በመሆኑ ጃፓን ለኢትዮጵያ ልማትና እድገት ድጋፏን እያሳየች ስለመሆኗ ለዳይሬክተር ጄኔራሉ ገልፀዉላቸዋል፡፡

ጃፓን የኢትዮጵያን ሰላም ማስከበር ተሳትፎ ለማጠናከር በሚሰሩ የአቅም ግንባታ ስራዎችም በቋሚነት እየደገፈች መሆኗን እና በቀጣይነትም በማዕከሉ በሚናከናውነው የአቅም ግንባታ ስልጠና ድጋፏን እንደምትቀጥል ያላቸዉን እምነት ሜጄር ጄኔራል አዳምነህ ምንግስቴ ገልፀዋል፡፡

በሰላም ማስከበር ማዕከል የአለም አቀፍ ሰላም ማስከበር ማሰልጠኛ ተቋም አዛዥ ብ/ጄኔራል ሰብስቤ ዱባ ለልኡካን ቡድኑ የኢትዮጵያን የሰላም ማስከበር ተሳትፎና የማዕከሉን ሚና እንዲሁም በማሰልጠኛ ተቋሙ እየተከናወኑ ስላሉ የትምህርትና ስልጠና ስራዎች ውጤቶችና ተግዳሮቶች ዙሪያ ማብራሪያ አድርገዋል፡፡

የጃፓን አለም አቀፍ የሰላም ትብብር ሴክሬታሪያት ዳይሬክተር ጄኔራል ሚስተር ካኖ ታኬሮ የተማሪዎችን ማረፊያ፣የመማሪያ ክፍሎችን፤የሁለተኛ ዲግሪ ተማሪዎችን የትምህርት አሰጣጥን እና የተማሪዎችን ተሳትፎ ከተመለከቱ በኋላ በማሰልጠኛ ተቋሙ እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን አድንቀዋል፡፡

ዳይሬክተሩ የጃፓን መንግስት የሚያደርገዉን ድግፍ እንደሚቀጥለበት ገልጸዉ ኢትዮጵያ በአለም አቀፍ ሰላም ማስከበር ተሳትፎ ያላትን የላቀ አስተዋፅኦ ሌሎች ሀገራት ሊቀስሙት እንደሚገባም ተናግረዋል፡፡በመጨረሻም የሁለቱን ሀገሮች የሚወክል የስጦታ ልውውጥ አድርገዋል፡፡

ግርማቸው አብርሀ

ፎቶግራፍ ሜቲ ጌታቸው

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ