በሶማሊያ የተሰማራው ሴክተር ሶስት የኢትዮጵያ የሰላም አስከባሪ ሀይል በሙሉ የዝግጁነት ቁመና ላይ እንደሚገኝ ተገለፀ፡፡

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

ህዳር 8 ቀን 2015 ዓ.ም

በሶማሊያ የተሰማራው ሴክተር ሶስት የኢትዮጵያ የሰላም አስከባሪ ሀይል በሙሉ የዝግጁነት ቁመና ላይ እንደሚገኝ ተገለፀ፡፡

በሶማሊያ በግዳጅ ላይ የሚገኘው የ7ኛ ዙር የሴክተር ሶስት የሰላም አስከባሪ ሀይል ያለው ወታደራዊ ዝግጁነት እና የተልዕኮ አፈፃፀም በአትሚስ የኢንስፔክሽን ቡድን በፍተሻ ተረጋግጧል፡፡

በተደረገው የኢንስፔክሽን ፍተሻም ሴክተሩ የታጠቃቸው ትጥቆችና የሚገለገልባቸው ንብረቶች በተሟላ ዝግጁነት ላይ እንደሚገኙና ማንኛውንም ግዳጅ ለመወጣት እንደሚያስችሉት መታዘባቸውን የአትሚስ የኢንስፔክሽን ቡድን መሪ አቶ ጀምስ ነስነሳህ ማረጋገጥ መቻላቸውን ተናግረዋል፡፡

የሴክተር ሶስት ሁለ-ገብ ሎጄስቲክ አዛዥ ኮ/ል አሰፋ አርጎ ሴክተሩ የታጠቃቸው አጠቃላይ ንብረቶች አትሚስ በሚፈልገው እና በሚጠይቀው ዝግጅነት ላይ መገኘቱን ገልፀው ፤ በቀጠናው ውጊያ ካጋጠመም በአጭር ጊዜ እና በአነስተኛ ኪሳራ ለማሸነፍ የሚያስችል ቁመና ላይ እንደሚገኙ አረጋግጠዋል፡፡

ሀብታሙ ገመቹ

ፎቶግራፍ አብዱልውሀብ ሙህዲን