ከመከላከያ ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት በወቅታዊ የፀጥታ ጉዳዮች ዙሪያ የተሰጠ ማብራሪያ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

ሰኔ 21 ቀን 2014 ዓ.ም

ከመከላከያ ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት በወቅታዊ የፀጥታ ጉዳዮች ዙሪያ የተሰጠ ማብራሪያ

ሰሞኑን በሱዳን ሰራዊት ቃል አቀባይ የተሰጠውን የተሳሳተ መግለጫ በማስመልከት የመከላከያ ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮሎኔል ጌትነት አዳነ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ከፍተኛ መኮነኑ ድርጊቱን በማስመልከት በመከላከያ ጠቅላይ መምሪያ ለጋዜጠኞች በሰጡት ማብራሪያ ኢትዮጵያ ከሱዳን ህዝብ እና መንግሥት ጋር ያላት መልካም ግንኙነት ረጅም አመታትን ያስቆጠረ ከመሆኑም ባሻገር የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ታሪካዊ በሆነው የሱዳን የአብዬ የሰላም ማስከበር ተልእኮ በሡዳንና በደቡብ ሡዳን ሀገሮች የተመረጠ በመሆኑ በአለም የሰላም ማስከበር ተልዕኮ ላይ ታማኝነቱ ይበልጥ ጎልቶ እንድታይ አድርጎታል።

ይሁን እንጅ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የሱዳን መንግሥት ከሽበርተኛው የህወሀት ቡድን ጋር በተናበበ መልኩ የሱዳን ወታደሮች የኢትዮጵያን ድንበር አልፈው እስከ መውረር የዘለቀ የሁለቱን ህዝቦች የእርስ በእርስ ግንኙነት የማይመጥን ተግባር ከመፈፀሙ በላይ ፀብ አጫሪ መግለጫ ሰጥቷል።

ዛሬም ድረስ የሱዳን ወታደሮች የኢትዮጵያን ድንበር አልፈው በመግባት ለሰው ህይወት መጥፋት ምክንያት ቢሆኑም በቀጠናው ለደረሰው የሰው ህይወት መጥፋት የተሰማንን ሀዘን እየገለፅን የመከላከያ ሰራዊታችን ግዳጁን በህግና በደንብ የሚወጣ ጀግና መሆኑ እየታወቀ የሠራዊቱን ስም በሀሠት የሚያጠለሹ አካላት ከድርጊታቸው ሊታቀቡ ይገባል።

በሠራዊታችን ላይ የሚነዛ የሀሠት ፕሮፖጋንዳን በማስመልከት እውነቱን ለማወቅ አጣራለሁ ለሚል ማንኛውም አካል በትብብር ለመስራት ዝግጁ መሆናችንን እንገልፃለን።

በተጨማሪም መንግስታችን ከሱዳን ጋር ያለውን የቀጠና ውጥረት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የሚያደርገውን ጥረት እያደነቅን ሰራዊታችን አሁንም ቢሆን ትእዛዝ ከተሰጠው እንደ ሽፍታ ሳይሆን በመደበኛ ውጊያ በአጭር ጊዜ ውስጥ ለማስወጣት በሙሉ ቁመና ላይ ይገኛል ።

ፍቅሩ ከበደ

ፎቶግራፍ እፀገነት ደቢሳ