የሰላም ስምምነቱ በታቀደለት መንገድ እንዲፈጸም መንግሥት እየሠራ ነው - የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

ህዳር 3 ቀን 2015 ዓ.ም

የሰላም ስምምነቱ በታቀደለት መንገድ እንዲፈጸም መንግሥት እየሠራ ነው - የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

በደቡብ አፍሪካ የተፈረመው የሰላም ስምምነት በታቀደለት መንገድ እንዲሄድ ለማድረግ የኢትዮጵያ መንግሥት እየሠራ ነው።

በዚህም መሠረት በመከላከያ ሥር ወዳለው አብዛኛው የትግራይ አካባቢ ርዳታ እንዲደርስ እየተደረገ ነው።

ወደተለቀቁት አካባቢዎች መሠረታዊ አገልግሎቶች ቀስ በቀስ እየተጀመሩ ነው።

በሌሎች አካባቢዎች አገልግሎቶችን ለማስጀመር እንዲቻል በታጣቂዎች የወደሙ መሠረተ ልማቶችን ለመጠገን ምቹ ሁኔታ እየተፈጠረ ነው።

ከዚሁ ጎን ለጎን በሰላም ስምምነቱ መሠረት የሕወሐት ታጣቂዎች ትጥቅ የሚፈቱበት ዝርዝር ዕቅድ ላይ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት አዛዥና የሕወሐት ታጣቂዎች አዛዥ በናይሮቢመክረዋል።

በሰላም ስምምነቱ በተያዘው የጊዜ ገደብ ትጥቅ የሚፈታበትንና መከላከያ ወደ መቀሌ የሚገባበትን ዕቅድ ላይም ተስማምተዋል።

ዕቅዱም በቀጣይ ተግባራዊ ይደረጋል። ለዕቅዱ ተግባራዊነት የሚመለከታቸው አካላት ሁሉ በስምምነቱ መሠረት የሚጠበቅባቸውን ሊወጡ እንደሚገባ መንግሥት ያሳስባል።

ህዳር 3 ቀን 2015 ዓ.ም

አዲስ አበባ

የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት