ሰራዊት እና ሀገር ግንባታ የተሰኘው መፅሀፍ በመከላከያ አዛዥነት እና ስታፍ ኮሌጅ የጥናት እና ምርምር ትምህርት ክፍል ኃላፊ በሆኑት በ ዶ/ር ስራው ደማስ ተዘገጅቶ ዛሬ ተመርቋል።

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

ሰኔ 18 ቀን 2014 ዓ.ም

"ሰራዊት እና ሀገር ግንባታ" የተሰኘው የ ዶ/ር ስራው ደማስ መፅሀፍ ተመረቀ።

ሰራዊት እና ሀገር ግንባታ የተሰኘው መፅሀፍ በመከላከያ አዛዥነት እና ስታፍ ኮሌጅ የጥናት እና ምርምር ትምህርት ክፍል ኃላፊ በሆኑት በ ዶ/ር ስራው ደማስ ተዘገጅቶ ዛሬ ተመርቋል።

መፅሀፉ በኢትዮጵያ የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ያለውን ሚና የሚያብራራ ነው።

ዶ/ር ስራው ደማስ እንደተናገሩት ለመከላከያ ሰራዊቱ ግንባታ የተፃፈ ቢሆንም ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ የመከላከያ ሰራዊት በሀገር ግንባታ ሂደት ያስቀመጠውን መልካም አሻራ ለማስተዋወቅ እና ለትውልዱ ታሪክ ለማስተላለፍ ታስቦ ነው።

የባህር ኃይል ዋና አዛዥ ሪል አድሚራል ክንዱ ገዙ በፕሮግራሙ ላይ ተገኝተው በሰጡት አስተያየት የህውሃት ባለ ስልጣናት መከላከያን እንደምሽግና እንደ ማስፈራሪያ በመጠቀም የህዝቡንና የሰራዊቱን ግንኙነትን በማሻከር ህዝባዊ አደራቸውን በአግባቡ ሳይወጡ መቅረታቸውን እና ህዝቡ ለውትድርና ያለው አመለካከት እንዲዋዥቅ አድርጎት እንደነበር በመፅሀፉ በግልፅ መጠቀሱን አድንቀዋል።

የኢትዮጲያ መከላከያ ሰራዊት ያልተነገሩ የጀግንነት እና መልካም ተግባር ለመጭው ተውልድ ተሰንዶ እንዲቆይ መፅሐፉ ትልቅ ድርሻ እንደሚያበረክትም ተገልጿል።

በረከት አዳነ

ፎቶግራፍ አቢዮት ዋሚ