የምዕራብ ዕዝ የሀገራችንን ክብርና ነፃነት ለማስጠበቅ የሚያስችል ቁመና መገንባቱን የዕዙ ዋና አዛዥ ተናገሩ።

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

ሰኔ 3 ቀን 2014 ዓ.ም

የምዕራብ ዕዝ የሀገራችንን ክብርና ነፃነት ለማስጠበቅ የሚያስችል ቁመና መገንባቱን የዕዙ ዋና አዛዥ ተናገሩ።

የዕዙ ዋና አዛዥና የአድዋ ሜዳይ ተሸላሚ ክቡር ሌ/ጀኔራል መሰለ መሰረት ከሻለቃ አዛዦች በላይ ካሉ የዕዙ የአመራር አካላት ጋር ባደረጉት ውይይት እንደተናገሩት አሁን ላይ ዕዛችን የመሳሪያ እና የሰው ሀይል የዝግጁነቱን በሚገባ አጠናክሯል።

ምዕራብ ዕዝ የአሸባሪው የህወሃት ጁንታን ሀገር የማፍረስ ህልም በሚገባ በማክሸፍ በውስን ክፍለጦሮች አከርካሪውን የሰበረ ጠንካራ ዕዝ ስለመሆኑ አውስተው አሁን ላይ ያለውን የሰው ኃይልና የትጥቅ ዝግጁነቱን በብዙ እጥፍ በማሳደግ ለሚሰጠው የትኛውም አይነት ተልዕኮ ዝግጁ ሆኖ በተጠንቀቅ ላይ ይገኛል ብለዋል።

በየትኛውም መንገድ የሰራዊታችንን ውስጣዊ አንድነት ለመሸርሸር የሚሰራ ማንኛውም እኩይ ሃይል ሰራዊታችንን ከተሰለፈበት ተልዕኮ ገሸሽ እንደማያደርገው ተናግረዋል።

ዋና አዛዡ ሌ/ጀኔራል መሰለ መሰረት ምዕራብ ዕዝ ለሀገሩ ህልውና ዋጋ መክፈልን ክብሩ አድርጎ ለተጨማሪ ታሪክ እና ድል የተዘጋጀ ጠንካራ ኃይል ስለመሆኑም አብራርተዋል።

ሰለሞን ሁነኛው

ፎቶግራፍ ሰለሞን ሁነኛው