በሽብርተኛው የሸኔ ታጣቂ ሃይል ጉዳት የደረሰበት የመልካ ጉባ ድልድይ መገንባት ዘርፈ ብዙ ወታደራዊ ጠቀሜታዎች እንዳሉት በቦታው የሚገኙ የፀጥታ ተቋማት አመራሮች ተናገረዋል።

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

ሰኔ 2 ቀን 2014 ዓ.ም

ዘርፈ ብዙ ወታደራዊ ጠቀሜታ ያለው የመልካ ጉባ ድልድይ ተገንብቶ ተጠናቀቀ።

በሽብርተኛው የሸኔ ታጣቂ ሃይል ጉዳት የደረሰበት የመልካ ጉባ ድልድይ መገንባት ዘርፈ ብዙ ወታደራዊ ጠቀሜታዎች እንዳሉት በቦታው የሚገኙ የፀጥታ ተቋማት አመራሮች ተናገረዋል።

የድልድዩ መሰራት ሰራዊቱ በዳዋ ወንዝ ሙላት ምክንያት ከቦታ ቦታ ተንቀሳቅሶ ግዳጅ ለመፈፀም የነበረበትን ተግዳሮት የፈታ የግንባታ ሂደት መሆኑም ተጠቅሷል።

በደቡብ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ ብርጌድ አዛዥ የሆኑት ኮሎኔል ብርሃነ ልጃለም እንዳሉት ከዚህ ቀደም የሸኔን ታጣቂ ሃይል ለመደምሰስ በተደረገው ዘመቻ የዳዋ ወንዝ ከፍተኛ ለተልዕኮ ችግር እንደነበር አውስተው የድልድዩ ግንባታ ፈጣን፣ ተወርዋሪና በሁሉም ቀጠናዎች ተንቀሳቅሶ ለድል የሚበቃ ሰራዊት የመገንባት አንድ አካል ተደርጎ ይወሰዳል ብለዋል።

በዕዙ የሬጅመንት አዛዥ የሆኑት ሻለቃ ገበረ ጋሞ በበኩላቸው ግንባታው የሰራዊታችን ድካም በመቀነስ በአጭር ጊዜ ውስጥ ተልዕኮን በብቃት የመወጣት ስራ የሚያቀላጥፍ ከመሆኑ ባሻገር የሶማሌና የኦሮሚያ አጎራባች ህዝቦችን ልማታዊ ትስስር የበለጠ የሚያጠናክር እንደሆነ ተናግረዋል።

ለአመታት አስቸጋሪ የመሬት ገፆችን እንደምሽግ በመጠቀም የሽብር ስራውን ሲያከናውን የቆየውን የሸኔ ቡድን ለመደምሰስ ቅንጅታዊ ስራ ተግባራዊ መደረጉ ለተገኘው ድል ወሳኝ ሚና እንደተጫወተ የሚናገሩት በኦሮሚያ ልዩ ሃይል የሬጅመንት አዛዥ ኢንስፔክተር ጅብሪል አደም በዘመቻው ወቅት ፈተና የነበረው የዳዋ ወንዝ ሙላት አሁን ላይ በተረጋገጠው ሰላም የድልድይ ግንባታ ተሰርቶለት መላው የፀጥታ ሃይል ለቀጣይ ተልዕኮ ዝግጁ መደረጉን አስረድተዋል።

በኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን የተገነባው ይህ የብረት ድልድይ የሶማሌ ክልል ዳዋ ዞንን እንዲሁም የኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ጉጅና ቦረና ዞኖችን የሚያዋስን ነው።

አበበ ሰማኝ

ፎቶግራፍ አበበ ሰማኝ