የ15ኛ ሞተራይዝድ ሰላም አሰከባሪ ሻለቃ በደቡብ ሱዳን ምዕራብ ኢኳቶሪያ ያምቢዮ ከተማ ለሚገኘው የህዝብ ሆስፒታል የተለያዩ መድኃኒቶች ድጋፍ አደረገ።

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

ሰኔ 2 ቀን 2014 ዓ.ም

የ15ኛ ሞተራይዝድ ሰላም አሰከባሪ ሻለቃ በደቡብ ሱዳን ምዕራብ ኢኳቶሪያ ያምቢዮ ከተማ ለሚገኘው የህዝብ ሆስፒታል የተለያዩ መድኃኒቶች ድጋፍ አደረገ።

በድጋፍ አሰጣጥ መርሀ ግብሩ ላይ የ15ኛ ሞተራይዝድ ሰላም አሰከባሪ ሻለቃ ደረጃ አንድ ሆሰፒታል ሜዲካል ኦፊሰር ሻለቃ ዶክተር ኃይሉ ቢሰውር እንደተናገሩት ሆሰፒታሉ ቀደም ሲል በአካባቢው በተከሰተው የእርስ በርስ ግጭት የወደመ በመሆኑ ወደቀደመው ስራ እንዲመለስ ለማድረግ ነው።

በቀጠናው በተፈጠረው ተነፃፃሪ ሰላም ምክንያት በርካታ የአካባቢው ነዋሪዎች ወደ ቄያቸው እየተመለሱ መሆናቸውን ተከትሎ ሆሰፒታሉ ያለበትን አጥረት ለማገዝ የተለያየ ዓይነትና ይዘት ያላቸው መድኃኒቶች ድጋፍ መደረጉን ሻለቃ ዶክተር ኃይሉ ቢሰውር ገልፀዋል።

የያምቢዮ ከተማ ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተር

ዶክተር በሽር አግሪ በበኩላቸው የኢትዮጵያ ሰላም

አሰከባሪ ኃይል የአካባቢያችንን ሰላምና ደህንነት

ከመጠበቅ ባሻገር የአካባቢው ህብረተሰብ በመደኃኒት ዕጦት አንዳይጎዳ በማሰብ ከራሱ ሬሸን ቀንሶ ላበረከተው ሰብዓዊነት የተሞላበት ድጋፍ በማህበረሰባችን ስም ልባዊ ምስጋና አቀርባለሁ ብለዋል።

ታደሰ ታምራት

ፎቶግራፍ ሠለምን ጌታቸው