በአትሚስ ሴክተር 6 ኢንስፔክሽን ቡድን መሪ አቶ መሃመድ ቢያሎ የተመራው ልዑክ የ5ኛ ሞተራይዝድ ሻለቃን የዝግጁነት ሁኔታ አረጋገጠ፡፡

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

ሰኔ 3 ቀን 2014 ዓ.ም

በአትሚስ ሴክተር 6 ኢንስፔክሽን ቡድን መሪ አቶ መሃመድ ቢያሎ የተመራው ልዑክ የ5ኛ ሞተራይዝድ ሻለቃን የዝግጁነት ሁኔታ አረጋገጠ፡፡

ቡድኑ የሻለቃዋን የሰው ሃይል፣ ወታደራዊ ተሸከርካሪዎች፣ ለግዳጅ አስፈላጊ የሆኑ ተተኳሾች፣ የሰራዊቱን መኖሪያና ሌሎች ንብረቶችን ፍተሻ በማድረግ ዝግጁነቱን አረጋግጧል፡፡

የሻለቃው ዋና አዛዥ ኮ/ል አሰፋ መኮነን ሰራዊቱ የተሟላ ዝግጅነቱን አጠናክሮ ሀገርን የሚያኮራ ግዳጅ እየተወጣ መሆኑን ጠቁመው ሁሉም የሻለቃዋ አባላት ላበረከቱት አስተዋፅኦ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

የሞተራይዝድ ሻለቃዋ ኢንስፔክሽን ሃላፊ ሻ/ል ሃብታሙ አያና እንዳሉት የተሰጠንን ሃላፊነትና ግዳጅ በብቃት ለመወጣት የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን በመፍታት በቁርጠኝነትና በጠንካራ ወታደራዊ ድስፕሊን አኩሪ ገድል ለመፈፀም በሁሉም መልኩ ዝግጁነታችንን ማረጋገጥ ይገባል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

አወል መሃመድ

ፎቶ ግራፍ አወል መሃመድ