የደቡብ ዕዝ ሜንቴናንስ መምሪያ በህግ ማስከበር ዘመቻው ከዕዙ አልፎ በግንባሩ ለተሰለፈው የመከላከያ ሃይል በሙሉ ፈጣን የጥገና አገልግሎት በመስጠት ከፍተኛ ድጋፍ ማድረጉ ተመለከተ ።

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

ሚያዝያ 5 ቀን 2013

ደቡብ ዕዝ ሜንቴናንስ መምሪያ በህግ ማስከበር ዘመቻው ከዕዙ አልፎ በግንባሩ ለተሰለፈው የመከላከያ ሃይል በሙሉ ፈጣን የጥገና አገልግሎት በመስጠት ከፍተኛ ድጋፍ ማድረጉ ተመለከተ ።
 
የደቡብ ዕዝ ምክትል አዛዥ ለሎጀስቲክስ ብ/ጄ ኢተፋ ራጋ ፣ የዕዙ ሜንቴናንስ መምሪያ በራያ ግንባር በነበረው የህግ ማስከበር ዘመቻ በግንባሩ የተሰለፈውን የየትኛውንም ክፍል ተሽከርካሪና የጦር መሳሪያ ድንገተኛ ብልሽት ሲያጋጥም ፈጥኖ ወደ ሃይል በመመለስና ግዳጁን ስኬታማ በማድረግ በኩል የራሱን የጎላ ሚና ተጫውቷል ብለዋል። የዕዙ ሜንቴናንስ አመራርና አባላት ፣ ልዩ የውጊያ ጊዜ ስልት በመንደፍ ጊዜና ቦታን ሳይመርጡ ከቆቦ እስከ መቀሌ ድረስ በመዘርጋት ዕዙን ብሎም በግንባሩ ለተሰለፈው ሃይል ፈጣን የጥገና አግልግሎት በመስጠት ለውጊያው
ትልቅ ድጋፍ ሰጥተዋል ፣ ለዚህ ተግባራቸውም ሊመሰገኑ ይገባቸዋል ብለዋል።
 
የዕዙ ሜንቴናንስ መምሪያ ሃላፊ ተወካይ ኮ/ል ሚልኪ ወጊ በበኩላቸው ፣ ሜንቴናንስ መምሪያው የውጊያ ተንቀሳቃሽ ጋራጅ በማቋቋም እውክታ ያጋጠማቸውን ቀላልና ከባድ የጦር መሳሪያዎች እና ተሽከርካሪዎች ቦታው ድረስ በመገኘት ፈጣን የጥገና አገልግሎት በመስጠትና በቶሎ ወደ ሃይል እንዲመለሱ በማድረግ ዘመቻውን በመደገፍ ትልቅ አስተዋፅኦ አበርክቷል ብለዋል።  መምሪያው በተሟላ የመጠገኛ ስፍራ ሊሰሩ የሚገባቸውን ተሽከርካሪዎች ጭምር በሌሊትና በቀን በቆሙበት በረሃማ ቦታ ሞተራቸውን በማውረድና የአካል ክፍላቸውን ቀጥቅጦ በመስራት ስኬታማ የሆነ ተግባር ተከናውኗል ብለዋል።
 
በጠቅላላው በግንባሩ ለተገኘው ውጤት በዕዙ ስር የሚገኙ የክ/ጦር ሜንቴናንሶች ድርሻም ከፍተኛ እንደነበር ተወካይ ሃላፊው ጠቁመዋል።
የዕዙ ሜንቴናንስና አባላቱ ለዚህ አኩሪ ተግባራቸው በመከላከያም ምስጋና ተቸሯቸዋል ሲሉ ኮ/ል ሚልኪ ወጊ ተናግረዋል።