ለህብረት ትምህርትና ስልጠና ዋና መምሪያ ስታፍ አባላት እንዲሁም በስሩ ለሚገኙ የትምህርትና ስልጠና ተቋማት የሰራዊት አባላት የማእረግ እድገት ተሰጠ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

ሚያዝያ 4 ቀን 2013

ለህብረት ትምህርትና ስልጠና ዋና መምሪያ ስታፍ አባላት እንዲሁም በስሩ ለሚገኙ የትምህርትና ስልጠና ተቋማት የሰራዊት አባላት የማእረግ እድገት ተሰጠ ::

በዋና መምሪያው የማእረግ እድገት ያገኙት የበታች ሹም ፣ መስመራዊ መኮንኖችና ከፍተኛ መኮንኖች ሲሆኑ ፣ በስራ አፈጻጸማቸው የላቀ ውጤት ያመጡና የቆይታ ጊዜያቸውን የሸፈኑ ናቸው::

ለተሿሚዎቹ ማእረግ ያለበሱትና የስራ መመሪያ የሰጡት የህብረት ትምህርትና ስልጠና ዋና መምሪያ ሀላፊ ሌተናል ጀነራል ሀሰን ኢብራሂም ናቸው::

ጀነራል መኮንኑ በሰጡት የስራ መመሪያ የማእረግ ሹመት የሚሰጠው በወታደራዊ ፕሮፌሽናሊዝምና ሳይንስ ምዘና ነው:: ፕሮፌሽኑ የሚጠይቀውን ክህሎት እና አስተሳሰብን ሟሟላትን ይጠይቃል ፡፡ ይህም ማለት ህዝብን እኩል ማየትና ማገልገልን ጨምሮ ሰላሙንና ልማቱን የራስ አድርጎ ማየት ያስፈልጋል::

ሰራዊታችን እንኳን ለራሱ ህዝብ በሰላም ማስከበር በተሰማራባቸው ቦታዎች ሁሉ ከራስ በፊት ለህዝና ለሀገር በሚለው እሴቱ ህዝብን እኩል የሚመለከትና የሚያገለግል ሀይል ነው ብለዋል ፡፡ ተሿሚዎችም የተቋሙን እሴት የመጠበቅና የመገንባት ድርብ ሀላፊነት የተሰጠቸው መሆኑን ገልጸዋል::

በእለቱ የማእረግ እድገቱን በተመለከተ ሪፖርት ያቀረቡት የህብረት ትምህርትና ስልጠና ዋና መምሪያ የሰው ሀብት መምሪያ ሀላፊ ኮሎኔል መኮንን መንግስቴ ናቸው::

መንግስቱ አበበ

ፎቶግራፍ እጸገነት ዴብሳ