ከመከላከያ ሰራዊታችን ህዝባዊነት ፣ ስነ-ምግባር እና የዓላማ ፅናትን ሌሎች የፀጥታ ሃይሎች ቢማሩ የተሰጣቸውን ተልዕኮ በአግባቡ መወጣት ያስችላቸዋል

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

ሚያዝያ 4 ቀን 2013

ከመከላከያ ሰራዊታችን ህዝባዊነት ፣ ስነ-ምግባር እና የዓላማ ፅናትን ሌሎች የፀጥታ ሃይሎች ቢማሩ የተሰጣቸውን ተልዕኮ በአግባቡ መወጣት ያስችላቸዋል ሲሉ የድሬድዋ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አለሙ መገራ ተናገሩ፡፡

መከላከያ ሰራዊታችን ከራስ በፊት ለህዝብና ለሃገር የሚለውን መርህ በተግባር እያስመሰከረ ያለ ፣ በድስፕሊንና በመርህ የሚመራ ሃይል በመሆኑ የድሬድዋ ከተማ የፀጥታ ሃይሎች ተሞክሮውን በመውሰድና ከምስራቅ ዕዝ የሰራዊት አባላት ጋር በትብብር በመስራት የከተማዋን ሰላምና ፀጥታ ማስከበር ችለናል ብለዋል፡፡

ኮሚሽነር አለሙ አያይዘውም ፣ የምስራቅ ዕዝ የ2ኛ ሜካናይዝድ አካል የሆነው 3ኛ ሞተራይዝድ 1ኛ ሻለቃ የሰራዊት አመራርና አባላት ፣ በአስተዳደሩ የተዋቀረው የፀጥታ ሃይል ጥምር ኮሚቴ አባል በመሆን በተቀናጀና በተናበበ መልኩ የቀጣዩ ስድስተኛ ሃገር አቀፍ ምርጫ ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ በጋራ እየሰራን እንገኛለን ሲሉ ተናግረዋል፡፡

የምስራቅ ዕዝ የ2ኛ ሜካናይዝድ 3ኛ ሞተራይዝድ 1ኛ ሻለቃ ም/አዛዥ ለሎጅስቲክስ ሻለቃ ዘላለም በቀለ ፣ ሰራዊታችን የተሰጠውን ተልዕኮ በብቃት እየተወጣ ሲሆን በአካባቢው ከሚገኙ ሌሎች የፀጥታ ሃይሎችና ከድሬድዋ ፖሊስ ጋር በመተሳሰር የአካባቢውን ሰላምና ደህንነት በአስተማማኝ ሁኔታ እያስከበርን እንገኛለን ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ዳንኤል አወል