የመከላከያ ሚኒስቴር የሠራዊት ግንባታ ስራዎች ዋና አስተባባሪ ሌተናል ጄኔራል ባጫ ደበሌ የጁንታው የጥፋት ሀይል በከፍተኛ ሁኔታ መደምሰሱን አረጋገጡ ።

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

ሚያዝያ 5 ቀን 2013

የመከላከያ ሚኒስቴር የሠራዊት ግንባታ ስራዎች ዋና አስተባባሪ ሌተናል ጄኔራል ባጫ ደበሌ ፣ የሽፍትነት ተግባር ለመፈፀም በተለያዩ የትግራይ አካባቢዎች ሲንቀሳቀስ የነበረው የጁንታው የጥፋት ሀይል በከፍተኛ ሁኔታ መደምሰሱን አረጋገጡ ።

በመቀሌና አካባቢው የሚገኙ ዋናና መጋቢ መንገዶች ላይ ለህዝቡና ለሰራዊቱ የሚንቀሳቀሱ የሎጂስቲክ ግብአቶቾን ለማስተጓጎል እና አለም አቀፍ ትኩረትን በውሸት ፕሮፓጋንዳ ለማግኘት አቅዶ በመንቀሳቀስ ላይ በነበረው የጁንታው የሽፍታ ሀይል ላይ በቴክኖሎጂ የታገዘ ከፍተኛ ጥቃት ተፈጽሞበት ተደምስሷል ብለዋል ፡፡

የተወሰኑ የሽፍታው አመራሮች ከቀሯቸው የተበታተነ ሀይል ውጭ ምንም አቅም የሌላቸው መሆኑን የገለፁት ጄኔራል መኮንኑ ፣ በከፍተኛ ተስፋ መቁረጥ ላይ የሚገኘው የጁንታው ቡድን የራሱን ቁስለኞች ሳይቀር ርህራሄ በሌለው መንገድ እየገደለ እንደሚገኝ ገልፀዋል።

ጁንታው በተለያዩ የትግራይ አካባቢዎች አነስተኛ ማሰልጠኛዎችን በመክፈት ለሶስት ቀናት ወታደራዊ ስልጠና በመስጠት ወደ ውጊያ ሊያስገባቸው የነበሩትን ሀይሎች መበተኑንና ማሰልጠኛዎቹም በመከላከያ ሰራዊታችን ሙሉ በሙሉ መደምሰሳቸውን ተናግረዋል።

ከሰራዊቱ የተረፉት የተወሰኑ የጁንታው አመራሮች በመሰባሰብ ከምዕራብ ትግራይ ወደ ሱዳን ለመሸሽ እየሞከሩ ቢሆንም ሰራዊታችን የማይደርስበት ፣ ጁንታው የሚያመልጥበት ቀዳዳ እንደሌለም አረጋግጠዋል።

ብዙአየሁ ተሾመ

ፎቶግራፍ ብዙአየሁ ተሾመ