ከሰሜን ሸዋ ዞን ደቡብ ወሎ ዞንና ኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር የተውጣጡ የህብረተሰብ ክፍሎች በዳዋ ጨፋ ወረዳ የሰላም ኮንፈረንስ አካሄዱ።

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]
ግንቦት 26 ቀን 2013
ከሰሜን ሸዋ ዞን ደቡብ ወሎ ዞንና ኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር የተውጣጡ የህብረተሰብ ክፍሎች በዳዋ ጨፋ ወረዳ የሰላም ኮንፈረንስ አካሄዱ።
በአካባቢው ዘላቂ ሰላምን ማረጋገጥና የህብረሰቡን አንድነት ማጠናከርን አላማው አድርጎ በሃይማኖት አባቶችና በሃገር ሽማግሌዎች አዘጋጅነት የተካሄው የሰላም ኮንፈረንስ የአንፆኪያ ገምዛ ወረዳ፣ የዳዋ ጨፋ ወረዳና የኬሚሴ ከተማ ነዋሪዎች ተሳትፈዋል።
በኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር በዳዋ ጨፋ ወረዳ በተረፍ ቀበሌ በተካሄደው የሰላም ኮንፈረንስ ላይ የኮማንድ ፖስቱ ሰብሳቢ ሌ/ጄ ደስታ አብቼ እና የመከላከያ ህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ኮ/ል ጌትነት አዳነን ጨምሮ የሰሜን ሸዋና የኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር የዞንና የወረዳ አመራሮች እንዲሁም የሰራዊቱና የፌዴራል ፖሊስ አመራሮች ተገኝተዋል።
ኮማንድ ፖስቱ በአሁኑ ሰአት የአካባቢውን ሰላም ለማረጋገጥ ከህብረተሰቡ ጋር በመተባበር በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝና የአካባቢው ሰላምም ወደቀደመ ሰላማዊ ሁኔታው መመለሱን የኮማንድ ፖስቱ ዋና አስተባባሪ ሌ/ጄ ደስታ አብቼ ገልፀዋል።
ሌ/ጄ ደስታ አብቼ አክለውም በአካባቢው ተከስቶ በነበረው ግጭት ተፈናቅለው የነበሩ ዜጎችን ወደቀደመ ስፍራቸው የመመለሱ ተግባር በትኩረት እየተከናወነና መሆኑን ጠቅሰው ወደ መኖሪያ አካባቢያቸው ያልተመለሱም ሙሉ በሙሉ ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ መልእክት አስተላልፈዋል።
በሰሜን ሸዋ ዞን የኦሮሞ ብሄረሰብ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አህመድ ሀሰንና የሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳደር የአደራጃጀት ዘርፍ ሃላፊ አቶ ዋሲሁን አበራ የግጭት ነጋዴዎችን በማክሰር ሀገርን ማሻገር የሁሉም ዜጋ ሃላፊነት በመሆኑ ሁሉም ባለ ድርሻ በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባው ተናግረዋል
የአንፆኪያ ገምዛ ፤የዳዋ ጫፋ ወረዳና የኬሚሴ ከተማ አስተዳደር አመራሮች በሰጡት አስተያየት ለአካባቢው ሰላም መረጋገጥ በትብብርና በቅንጅት እየሰሩ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
የአማራና የኦሮሞ ህዝቦች ለዘመናት ተዋደውና ተጋምደው የኖሩ ህዝቦች መሆናቸውን የሰላም ኮንፈረንሱ ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት ጠቅሰው ይህ ለዘመናት የቆየ አንድነት ተጠናክሮ እንዲቀጥል የበኩላቸውን እንደሚወጡ አረጋግጠዋል፡፡
ከውይይቱ በኋላም ለኮማንድ ፖስቱና ለፀጥታ አካላት ከነዋሪዎቹ የተለያዩ ስጦታ ተበርክቷል፡፡
 
ንጉሴ ውብሊቀር
ፎቶግራፍ ተሰማ ኡርጌሳ