በመከላከያ ሚኒስቴር የምድር ሀይል ጠቅላይ መምሪያ ከፍተኛ አመራሮች እና ሙያተኞች የብርሸለቆ መሠረታዊ ውትድርና ማሰልጠኛ ትምህርት ቤትን ጎበኙ ፡፡

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]
ሰኔ 7 ቀን 2013
በመከላከያ ሚኒስቴር የምድር ሀይል ጠቅላይ መምሪያ ከፍተኛ አመራሮች እና ሙያተኞች የብርሸለቆ መሠረታዊ ውትድርና ማሰልጠኛ ትምህርት ቤትን ጎበኙ ፡፡
በምድር ሀይል ጠቅላይ መምሪያ የጤና መምሪያ ሃላፊ ብ/ጀ ይልማ መኳንንት በጉብኝቱ ወቅት እንደተናገሩት ፣ ማሰልጠኛ ት/ቤቱ በተቋሙ ከተሰጠው ግዳጅ የሰው ሀይልን በብቃትና በጥራት ከማሰልጠን በተጨማሪ በተለያዩ የመሰረተ ልማት ስራዎች ላይም ትኩረት ሰጥቶ ትልቅ ስራ እየሰራ እንዳለ ተመልክተናል ፡፡ በሀገራችን አረንጓዴ አሻራ ለማሳረፍ በተደረገው እንቅስቃሴም የተተከሉ ችግኞችን በመንከባከብ ሰፊ ስራ ተሰርቷል ብለዋል፡፡
የማሰልጠኛ ት/ቤቱ ዋና አዛዥ ኮ/ል ጌታቸው አሊ በበኩላቸው ፣ የጀመርናቸውን ስራዎች በማጠናከር ይበልጥ በመስራት ተልዕኳችንን በሚገባ እንወጣለን ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ስለትምህርት ቤቱ አጠቃላይ ሁኔታ በማሰልጠኛው ፅህፈት ቤት ሃላፊ ሻለቃ ፍቅሬ ዳመና በፅሑፍና በምስል ገለፃ የተካሄደ ሲሆን ፤ የሰልጣኝ መኖሪያ ሰፈር ፣ ቢሮዎች ፣ የስልጠና ወረዳዎች ፣ ደረጃ 2 ሆስፒታል እንዲሁም ዳቦ ቤት ጉብኝት ተካሂዷል። ማሰልጠኛ ት/ቤቱ በርካታ ውጤታማ ስራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝም ተጠቁሟል::
ውዴ ዝጉ
ፎቶግራፍ አስናቀ አሞኘ