ሁለተኛው ዙር የመተከል ዞን የተሃድሶ ስልጠና ዛሬ ተጀምሯል። ለስልጠናው 1ሺ 620 ከዚህ በፊት ለውጡን ያልተቀበሉና ጫካ ገብተው የነበሩ ታጣቂዎች ማዕከሉ ገብተዋል።

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]
ሰኔ 4 ቀን 2013 ዓ.ም
ሁለተኛው ዙር የመተከል ዞን የተሃድሶ ስልጠና ዛሬ ተጀምሯል።
ለስልጠናው 1ሺ 620 ከዚህ በፊት ለውጡን ያልተቀበሉና ጫካ ገብተው የነበሩ ታጣቂዎች በዞኑ ከሚገኙ ወረዳዎች የተሃድሶ ስልጠናውን ለመውሰድ ወደ ማዕከሉ ገብተዋል።
በስልጠናው መክፈቻ ስነ ስርዓት ላይ የኮማንድ ፖስቱ ሰብሳቢ ሌ/ጄ አስራት ዴኔሮ፣የቤኔሻንጉል ጉሙዝ ክልል ብልፅግና ፓርቲ የአደረጃጀት ዘርፍ
ኃላፊ አቶ መንግስቱ ቴሶ፣የዞንና የክልል ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም የሠራዊቱ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።
ካሁን ቀደም ቀይና ጥቁር እየተባለ በቀለም የሚደረገው ልዩነት ለዘመኑ የማይመጥን ንግግር ነው ተብሏል ።
በስልጠናው ሽፍታ የነበረው አሁን የሠላምና የልማት ኃይል እንዲሆን በሚያስችል መልኩ እንደሚሰጥለጥን ተገልጿል።
ቀደም ሲል በዞኑ በተፈጠረው ግጭት ምክንያት ተይዘው የነበሩ ወደ 43 የሚጠጉ ፕሮጀክቶች ሳይሰሩ ቀርተዋል።
የመጣውን ሰላም በዘላቂነት ለማስቀጠል እጅ ለእጅ ተያይዞ መሄድ እንደሚገባም ተጠቁሟል።
ዞኑን የብጥብጥና የትርምስ ቀጣና ለማድረግ የሚሯሯጡ ኃይሎች አሉ፤ ማንም የውጪ ኃይል ቢመጣ የኢትዮጵያ ህዝብ በተባበረ ክንዱ ይደመስሳቸዋል ። የጉምዝ ህዝብም የዚሁ ታሪክ አካል ነው ። በመሆኑም ውስጣዊ አንድነታችንን ማጠናከር ይገባልም ተብሏል።
ቀደም ሲል በአንደኛው ዙር ስልጠና አምስት መቶ የሚሆኑ ታጣቂ የነበሩ የተሃድሶ ስልጠና የተሰጣቸው ሲሆን ከነዚህ ውስጥ 98 ከመቶ የሚሆኑት አመራሮች እንደነበሩ የሚታወስ ነው።
ዳዊት እንዳለ
ፎቶግራፍ ዳዊት እንዳለ