በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ ግድምና ጅሌ ጥሙጋ ወረዳ በሚገኙ የማህበረሰብ ክፍሎች የጥፋት ኃይሎች በፈጠሩት ሴራ የተፈጠረው መቃቃር መከላከያ ሠረዊቱ በማሸማገል ችግሩን መፍታት ችሏል

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]
ሰኔ 7 ቀን 2013
በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ ግድምና ጅሌ ጥሙጋ ወረዳ በሚገኙ የማህበረሰብ ክፍሎች የጥፋት ኃይሎች በፈጠሩት ሴራ የተፈጠረው መቃቃር መከላከያ ሠረዊቱ በማሸማገል ችግሩን መፍታት ችሏል።
ሠራዊቱ የሀገርን ሉዓላዊነት ወደ ማስከበር ተልዕኮው አንዲመለስ የውስጡን ችግር እኛው መፍታት አለብን ሲሉም የሀገር ሽማግሌዎች ጥሪ አቅርበዋል።
በአጣየና አካባቢው የተፈጠረውን ሁከትና ብጥብጥ ለማስቆም ከፍተኛ የሠራዊቱ አመራርና አባላት ከአርሶ አደሩ ጓሮ ድረስ በመሄድ የሕዝቦችን አንድነት ለማምጣት እየሠሩ ነው።
ኢትዮጵያውያን ካላቸው አኩሪ እሴቶች አንዱ በባህላዊ መንገድ ግጭቶችን መፍታት ሲሆን በአጣዬና አካባቢው የተፈጠረውን ችግር ለመፍታት መከላከያ ሠራዊቱ በዛፍ ሥር ሕዝቦችን በማሰባሰብ ወደ ሠላም ድርድር አምጥቷል።
በአጣዬ የተቋቋመው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አስተባባሪ ሌ/ጄ ደስታ አብቼ ፣ አሁን ላይ ኢትዮጵያን የትርምስ ቀጣና ለማድረግ የሚፈልጉ ኃይሎች በየቀበሌው በመግባት አብሮነታችንን እና አንድነታችንን እያናጉ በመሆኑ ህዝቡ መንቃት አለበት ብለዋል።
ሽብር ፈጣሪዎችን ሕብረተሰቡ ለሕግ አጋልጦ መስጠት እንዳለበትም ተናግረዋል።
በዕርቅ መርሃ ግብር ላይ የተገኙት የሀገር ሽማግሌዎች በበኩላቸው ፣ መከላከያ ሠራዊት የሀገርን ዳን ድንበር ወደማስጠበቅ ተልዕኮው እንዲመለስ ሁላችንም ለሠላማችን ዘብ መቆም አለብን ብለዋል።
የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በአጣዬና አካባቢዋ ዳግም ግጭት እንዳይከሰት በሕዝቦች መካከል ቃለ መሐላ በማስፈፀም ሀገራዊ አደራውን እየተወጣ ይገኛል።
ውብሸት አንበሴ
ፎቶግራፍ ኃይሉ ፈዬ