ከኢፌዲሪ መከላከያ፣ ከፌዴራል እና ከአዲስ አበባ ፖሊስ ለተውጣጡ የሰራዊት አባላት በሶማሊያ የሰላም ማስከበር ተልዕኮ ዙሪያ (ATMIS) የሎጅስቲክ ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል፡፡

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

ሰኔ 2 ቀን 2014 ዓ.ም

ከኢፌዲሪ መከላከያ፣ ከፌዴራል እና ከአዲስ አበባ ፖሊስ ለተውጣጡ የሰራዊት አባላት በሶማሊያ የሰላም ማስከበር ተልዕኮ ዙሪያ (ATMIS) የሎጅስቲክ ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል፡፡

 

ስልጠናው የመከላከያ ሰላም ማስከበር ማዕከል አለም አቀፍ ሰላም ማስከበር ማሰልጠኛ ተቋምና የእንግሊዝ መንግስት በጋራ ባዘጋጁት በመከላከያ ሰላም ማስከበር ማዕከል ቅጥር ግቢ ለሁለት ሳምንታት ያህል እንደሚቆይ ተገልጿል፡፡

ለአባላቱ የሚሰጠው የሎጅስስቲክ ስልጠና ሰልጣኞች በሚሰማሩባቸው በተባበሩት መንግስታት የሰላም ማስከበር ተልዕኮ ሆነ በተመደቡበት የስራ ዘርፍ በሳይንሳዊ መንገድ ንብረት የማስተዳደር፣ የማጓጓዝ እና የመጠገን ስራዎችን በላቀ ሁኔታ መፈፀም በሚችሉበት መንገድ ጉልህ ሚና እንደሚኖረው ተገልጿል፡፡

ለአባላቱ ለሁለት ሳምንት የሚሰጠው የሎጅስቲክ ስልጠና በንድፈ ሃሳብና በተግባር ልምምዶችን ያካተተ እንደሆነም ተገልጿል፡፡

በመከላከያ ሰላም ማስከበር ማዕከል አለም አቀፍ ሰላም ማስከበር ማሰልጠኛ ተቋም አዛዥ ብ/ጄኔራል ሰብስቤ ዱባ በፕሮግራሙ መክፈቻ እንደገለፁት በሶማሊያ የሰላም ማስከበር ተልዕኮ ዙሪያ የሚሰጠው የሎጅስቲክስ ስልጠና ለሰልጣኞች የተሻለ አቅም እና ግንዛቤ ይፈጥራል።

በአፍሪካ ህብረት በአለም አቀፍ ሰላም ማስከበር ለሚሰማሩ የሰላም ማስከበር የሰራዊት አባላት የሎጅስቲክስ እቅድና ዝግጅት በዘመናዊና ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ ለመስራትና የተጠናከረና የተቀናጀ የሎጅስቲክ ድጋፍና የስምሪት ስራዎች መከወን እንዲቻል ከፍተኛ የሆነ አስተዋፅኦው እንዳለው ገልፀዋል፡፡

ግርማቸው አብርሃ

ፎቶግራፍ ሜቲ ጌታቸው