ድንበር በማይገድበው የህዝባዊነት ዕምነት ሌት ተቀን በመስራት የቀጣናችንን ሰላም ማረጋገጥ ችለናል ሲሉ የዘጠነኛ ዙር ሁለተኛ ታንከኛ ዋና አዛዥ ሻለቃ ቀጄላ ጨዋቃ ገለፁ።
ድንበር በማይገድበው የህዝባዊነት ዕምነት ሌት ተቀን በመስራት የቀጣናችንን ሰላም ማረጋገጥ ችለናል ሲሉ የዘጠነኛ ዙር ሁለተኛ ታንከኛ ዋና አዛዥ ሻለቃ ቀጄላ ጨዋቃ ገለፁ።
የታንከኛ ክፍሉ በግዳጅ ቀጣናው የመንገድ መሠረተ-ልማት እንዲስፋፋ፣ወታደራዊ ታዛቢዎች በነፃነት ተንቀሳቅሰው ተግባራቸውን እንዲያከናውኑ፣ተሽከርካሪዎች ያለስጋት እንዲንቀሳቀሱ ተገቢ ጥበቃ ማድረግ ችለናል ያሉት ዋና አዛዡ ፣ በተቻለ መጠን የአካባቢውን ህዝብ ማህበራዊ ችግሮች እንደ ንፁህ የመጠጥ ውሃ አቅርቦቶች በመሳሰሉ ለማቃለልም በትኩረት እየሠራን ነው ብለዋል።
ከፍተኛ መኮንኑ ፣ ክፍሉ የሜካናይዝድ ክፍል ቢሆንም ፣ ሁለገብ በመሆን የእግረኛን ስራ ጨምሮ እየተወጣ እንደሚገኝና ፣ የአባላቱ ጥንካሬም የሚደነቅ መሆኑን ጠቁመዋል።
የአባላቱ እና የአሽከርካሪዎቻችን የተቀናጀ እንቅስቃሴ ቀንም ሆነ ሌሊት በማንኛውም ሰዓት የሚፈጠርን ችግር ፈጥኖ በመድረስ መፍታት እንድንችል አድርጎናል ያለው ደግሞ ፣ የሁለተኛ ታንከኛ መገናኛና ስምሪት ሃላፊ የሃምሳ አለቃ ብሩክ አበራ ነው።
አስቻለው ሌንጫ
ፎቶግራፍ ብሩክ ጌታቸው