በኢ.ፌ.ዴ.ሪ አየር ኃይል ምክትል አዛዥ ለአየር መከላከል ፣ በአዲስ ዲዛይን ያሰራውን የምክትሉን መለያ አርማ እና ያስገነባውን አዲስ የአስፓልት መንገድ አስመረቀ፡፡

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

መለያ አርማውንና መንገዱን መርቀው በመክፈት የስራ መመሪያ ንግግር ያደረጉት የኢ.ፌ.ዴ.ሪ አየር ኃይል ዋና አዛዥ ሜ/ጀ ጀነራል ይልማ መርዳሳ ናቸው፡፡
አዛዡም በንግግራቸው ምክትሉ ለአየር ኃይላችን ውጤታማ የተልዕኮ አፈፃፀም ትልቅ አስተዋፅዖ ማበርከቱን አስታውሰው ፣ በተለይም በጁንታው ድንገተኛ ጥቃት የተበታተነውን የሰው ኃይልና የወደመውን የአየር መከላከያ መሳሪያዎችን በፍጥነት መልሶ በማደራጀት የህግ ማስከበር ዘመቻችን በድል እንዲጠናቀቅ ወሳኝ ሚና ተጫውቷል ብለዋል፡፡
አየር መከላከያችንን ለማዘመን በምክትሉ አመራሮችና አባላት ዘንድ አሁን የተጀመረው የስራ መነቃቃትና ቁርጠኝነት ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ያሉት ዋና አዛዡ ፣ የአየር ኃይል ኮማንድም እንደ ሁል ጊዜው ለምክትሉ የሥራ አፈፃፀም የተለያዩ ድጋፎችን ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በኢ.ፌ.ዴ.ሪ አየር ኃይል ምክትል አዛዥ ለአየር መከላከል ጊዜያዊ አዛዥ ኮ/ል ኃይሉ መኮንን ፣ አየር መከላከያ ካለበት የግዳጅ ቀጣና ስፋት አንፃር ሰፋፊ ስራዎችን ማከናወኑን ጠቁመው ፣ በዚህም ወቅታዊ ሁኔታውን ባገናዘበ መልኩ ሳይቶችን በመምረጥ ፣ የሰው ኃይል በማደራጀት ፣ በስልጠናና ጥገና በኩል በተሰራው አመርቂ ተግባር በአሁኑ ወቅት የምክትሉ የግዳጅ አፈፃፀም በሁሉም ረገድ የተሻለ ደረጃ ላይ ይገኛል ብለዋል፡፡
በእለቱም ህግ በማስከበር ዘመቻ የበኩላቸውን ለተወጡ ምክትሎች ፣ ምድቦችና መምሪያዎች እንዲሁም በስራ አፈፃፀማቸው ብልጫ ላመጡ የአርማ ስጦታና የእውቅና ሰርተፊኬት የተበረከተላቸው ሲሆን ፣ በአድስ ዲዛይን የተሰራ የምክትሉ መለያ አርማ እና የአስፓልት መንገድ በአየር ኃይል ዋና አዛዥና ኮማንድ በይፋ ተመርቆ ተከፍቷል፡፡
በኢ.ፌ.ዴ.ሪ አየር ኃይል ከሚገኙ አራቱ ክፍሎች አንዱ የሆነው ምክትል አዛዥ ለአየር መከላከል ፣ በማዕከላዊ ፣ በሰሜንና በምዕራብ እስከ ህዳሴው ግድባችን ሰፊውን የሀገሪቱን ክልል በመሸፈን የ24 ሰዓት የአየር ክልላችንን ጥበቃ የሚያከናውን ለአየር ኃይላችን ዋነኛው ድጋፍ ሰጪ ክፍል መሆኑ ተገልፃDል፡፡
ፍቅሬ በቀለ
ፎቶግራፍ ጽጌ ዳዊት