በደቡብ ሱዳን ጁባ እና አካባቢው የሚገኙ የ15ኛ ሞተራይዝድ ሠላም አስከባሪ ሻለቃ አባላት የተባበሩት መንግስታት ሠላም አስከባሪ ሰማዕታት መታሰቢያ ቀንን አስበው ዋሉ።

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]
ግንቦት 22 ቀን 2013
በደቡብ ሱዳን ጁባ እና አካባቢው የሚገኙ የ15ኛ ሞተራይዝድ ሠላም አስከባሪ ሻለቃ አባላት የተባበሩት መንግስታት ሠላም አስከባሪ ሰማዕታት መታሰቢያ ቀንን አስበው ዋሉ።
"የሰላም መንገድ በወጣቶች ይመራል" በሚል መሪ ቃል ዕለቱ ሲታሰብ የሻለቃው አባላትም ለአለም ሠላም መጠበቅ ሲሉ መስዋዕት ለሆኑ ጀግኖች የህሊና ፀሎት በማድረግ ዕለቱን አክብረዋል።
የሻለቃው ዋና አዛዥ ኮሎኔል ከፍያለው ረጋሳ በመልዕክታቸው ፣ በተባበሩት መንግስታት የሠላም ማስከበር ግዳጅ ላይ ተሰማርተው ሰማዕት የሆኑ ሲቪል እና የሰራዊት አባላት የከፈሉትን ዋጋ ታሪክ ሲዘክረው ይኖራል ብለዋል።
በአለም የሰላም ማስከበር ተልዕኮ ላይ ተሰማርተው አገልግሎት ለሰጡ እና እያገለገሉ ላሉ በሙሉ ለአላማቸው፣ለሙያቸውና ለጀግንነታቸው አድናቆትና ክብር ለመስጠት ዕለቱ መታሰቡ ትልቅ ትርጉም እንዳለው ነው የተገለፀው።
ኢትዮጵያ ለአለም ሠላም መከበር እየከፈለች ያለውን ዋጋ አጠናክራ ትቀጥላለች ያሉት ኮሎኔል ከፍያለው ረጋሳ የ15ኛ ሞተራይዝድ ሠላም አስከባሪ ሻለቃ አመራርና አባላትም በቀጣናው እየፈፀምን ያለውን ተልዕኮ በስኬት ልናስቀጥል ይገባል ሲሉ አስገንዝበዋል።
አስቻለው ኛኙኬ
ፎቶግራፍ ሠለሞን ጌታቸው እና ዝናሽ አደባ