የመከላከያ እግር ኳስ ጤና ቡድን የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ጤና ቡድንን 3 ለ 1 በማሸነፍ የዋንጫ አሸናፊ ሆነ።

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

ሰኔ 19 ቀን 2014 ዓ.ም

የመከላከያ እግር ኳስ ጤና ቡድን የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ጤና ቡድንን 3 ለ 1 በማሸነፍ የዋንጫ አሸናፊ ሆነ።

በአዲስ አበባ ስፖርት ለሁሉም ኮሚቴ አዘጋጅነት በተካሄደው 12ኛው የመስሪያ ቤቶች የጤና እግር ኳስ ውድድር የመከላከያ ጤና ቡድን ሁሉንም ጨዋታዎች በማሸነፍ የዋንጫ ባለቤት ሆኗል።

በአበበ ቢቂላ ስታዴየም በተደረገው የፍፃሜ ጨዋታ የመከለከያ እግር ኳስ ጤና ቡድን ተጫዋቾቹ ም/መ/አለቃ ደረጄ ግዛው፣ አስር አለቃ አንተነህ ጌታቸው እና አስር አለቃ ምስጋናው ሌንጫ በአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ጤና ቡድን ላይ ጎል አስቆጥረዋል።

በወድድሩ የመከላከያ ጤና ቡድኑ መ/አ ሰይፈ ታጁ ኮከብ ተጫዋች ሆኖ የተመረጠ ሲሆን የቡድኑ አሰልጣኝ ሻምበል ወንድወሰን በየነ ኮከብ አሰልጣኝ በመሆን የገንዘብና የሰርተፍኬት ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

ገረመው ጨሬ

ፎቶግራፍ ገረመው ጨሬ